ይህንን ዝማሬ እግዚአብሔር ለሁልችንም የመፅናናትና የመበርታት ምንጭ እንዲሆን ነው የሰጠን የሚል ሙሉ እምነት አለኝ! በየሐዋ 17:28 ከሚገኘው ሀሳብ ጋር ተያይዞ የተፃፈ ነው::
ይህንን ዝማሬ የፃፍኩት ከ13 ዓመት በፊት ገደማ ነው:: በእነዚህ ዓመታት ባሳለፍኩት መንገድ ሁሉ እግዚአብሔር ስለረዳኝ ዛሬ ይህንን መዝሙር መዘመር ልዩ ትርጉም ይሰጠኛል! እግዚአብሔር አሁንም ከፍ ይበል!
"አንተ ምስጋናዬ ነህ" የድሬደዋ መሰረተ ክርስቶስ "ሀ" መዘምራን መዝሙር ሲሆን "አፌን ሳቅ ሞልቶታል ደግሞ የጌታያውቃልና ብሩክታዊት መዝሙር ነው:: መጨረሻ ላይ የምዘምረው "ክበር ብልህ ያንስብህ...ባመሰግንህ እኔ አልጥግብም" ደግሞ የወ/ም ዐቢይ ሐዋዝ መዝሙር ነው::
ይህን ዝማሬ መዘመር ከከጀመሬ በፊት አጭርን ምስክርነት መስክሬ ነበር:: The congregation was so welcoming and eager to praise along! በዚህ መዝሙር ብዙ ፀጋን እንደምንካፈል አጠራጠርም:: "ሌሊቱ ነጋ" የወ/ም አውታሩ ከበደ መዝሙር ሲሆን "ሳሰላስለው" ደግሞ የወ/ም ተከስተ ጌትነት ዝማሬ ነው::
Copyright © 2020 ETANA - All Rights Reserved.